ቀደም ሲል በፋሲሊቲ ማኔጅመንት በሚል የሥራ ሂደት ውስጥ የነበረ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ራሱን ችሎ የጸቋቋመ ክፍል ነው፡፡ መስራቹም አቶ በጊዜው አበበ ሲሆን በሁለት ቡድን መሪዎች ሥር በተዋቀሩ 27 ሰራተኞችን በመያዝ የተሸከርካሪ ድልድል ስምሪትና ዝውውር የማድረግ የትራንስፖርት ሰርቪስ እና የጋራዥ ስምሪት የማደራጀት እንዲሁም የመድን ደህንነት ሽፋንና አመታዊ የተሸከርካሪዎች ጤንነትና ጥንካሪ ምርመራ የማድረግ ተግባር ይከውናል፡፡ ለተማሪዎች ክሊኒክ የ24 ስዓት የአምቡላንስ አገልግሎትም ይሰጣል፡፡