የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈጻሚያ ጽ/ቤት የዩኒቨርሲቲውን ሥራዎችና ጉዳዮች በተሻለ መንገድ ለማቀላጠፍ እንዲቻል የተቋቋመ ዘርፍ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ በዋናነት የሚከተሉትን ጉዳዮች ያከናውናል፡፡
- ከዩኒቨርሲቲው የሚመጡትን የበጀት ጥያቄዎች፣ ውጤቶችና ሪፖርቶች አደራጅቶ ለገንዘብ ሚኒስቴር ተገቢ ክፍሎች ያደርሳል፤ ውጤቱንም ተከታትሎ ለጽ/ቤቱ ያቀርባል፡፡
- የሚካሄዱ የግዥ፣ የተሽከርካሪ ጥገና እና እድሳት ሥራን ያስተባብራል፤
- ለዩኒቨርሲቲው ከውጭ ሀገር የሚገቡ እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ወደወጭ ሀገር የሚላኩ ዕቃዎችን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ድረስ በመሄድ ያስፈጽማል፤
- ዩኒቨርሲቲውን የሚመለከቱ አስተዳደር ጉዳዬችን ይከታተላል፤
- ከዋናው ግቢ ከሁሉም የሥራ ክፍሎች የሚሰጡ ተግባራት በመቀበል ተፈጻሚ ያደርጋል፤
Biniam Atirsaw
Coordinator
Mobile 091 396 7604
Email:-